ሰለ ድርጅታችን (EFCE)

የኢትዮጵያውያን ገንቢ የውይይት መድረክ

ቃላችን

የሰላም ማምጣት ሂደት አንድን እርምጃ በአንድ ጊዜ እንደመራመድ ሲሆን፤ ተስፋ መቁረጥ ግን አይመረጥም።

ራዕይ

ሰላማዊት ፣ ታዳጊ ፣ አንድነቷ የጠነከረና የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት

ተልእኮ

የሽምግልና ጥበብንና ሳይንስን በመጠቀም በኢትዮጵያውያን መካከል በሀገር

ውስጥና በዲያስፖራ  ለጋራ ጥቅም የሚበጅ ገንቢ የውይይት መድረክ እና ባህልን ማዳበር ፡፡

ግብ

በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በዲያስፖራ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር

ሠላምን ከሚያስፍኑ እና በሰላም ግንባታ ተግባር  ላይ ከሚሳተፉ ግለሰቦች ፣

ቡድኖችና ድርጅቶች በአንድነት አብሮ በመሆን ለበጎ ፈቃድ ፣ መተማመንና

የጋራ መግባባት እንዲስፋፋ ገንቢ የሆኑ ግንኙነቶችን የሚያካሂዱበት በኢትዮጵያ

የተለያዩ ፍላጎቶችና የፖለቲካ አመለካከቶች የሚስተናገዱበት፣ የተለያዩ የማህበረሰብ

ክፍሎች የሚሳተፉበት በመልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የጋራነትን የሚያጎለብት

ገንቢ የውይይት መድረክ እውን ማድረግ ፡፡

ዓላማዎች

የአጭርጊዜ ዓላማዎቻችን በዲያስፖራ ካሉ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲሁም ከኢትዮጵያ

ሽማግሌዎችና በቅርቡ ከተቋቋመው የእርቅና የሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር

በኢትዮጵያ ውስጥ የዴሞክራቲክ ለውጡንና የሽግግር ሂደቱን መደገፍ ይገኙበታል፡፡

የረጅምጊዜ ዓላማዎቻችን

  1. እንደኢትዮጵያያለብዝሃነት በልዩነት በሚታይባት ሀገር ውስጥ ለግል እድገት ፣ 

ለድርጅታዊ ስኬትና ለአገር ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ችሎታዎች በብሔራዊ  

ሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ እንዲካተት መርዳት፡፡  በትምህርታዊ 

ሥርዓተ‐ትምህርት ውስጥ መካተት የሚገባቸው የተወሰኑ ክህሎቶች 

ለምሳሌ ውህደትን መደገፍ፣ የግጭት አፈታት ፣ ድርድር ፣ አቻነት ላይ

የተመሠረተ  ሽምግልና ፣ ብልህነታዊ የስሜት  አያያዝ ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ 

እንዲሁም የግልና የድርጅታዊ ሥነ ምግባር ናቸው ፡፡

  1. ትምህርታዊ መርሃ ግብሩን በማጠናከር “እሷን ማስቻል” (“Enable Her”)

የሚል እቅድ አለን።እቅዱም፥ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ልጆች 

የወር አበባ መጠበቂያ ለራሳ አገዝ የማዘጋጀት ስልጠናን እና ትምህርን ማቅረብ። 

ይህንን ጥረት በስራ ላይ ለማዋል የውሃ ጉድጓዶችን ቁፈሮ ማደራጀት እና አብሮ

ማካሄድ ሌላው ተግባራችን ነው። (“እሷን ማስቻል”(“Enable Her”)

የእቅድን ዝርዝር መግለጫ በሰነዱ ክፍል በመሄድ ይረዱ )

  1. ለመጀመሪያናለድህረተመራቂተማሪዎች የሚያገለግሉ ለሁሉም የጥናት ዘርፎች

የሚውሉ የወረቀት እና የዲጂታል መጻሐፍትን ለሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች

ሰብስበን ማድረስ።

Share: